አቶ አገኘሁ ተሻገር የሰላም ግንባታና የሕዝብ ደህንነት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ የአቶ አገኘሁ ተሻገርን የክልሉ የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ሃላፋነት ሹመትን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

አቶ አገኘሁ ላለፉት 20 ዓመታት በክልሉ በልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች መስራታቸው ተገልጿል፡

ከሰላምና ጸጥታ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ልምድ ያላቸው በመሆኑ ለወቅቱ የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ሁኔታ መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

ዘገባው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡