የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነው በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ ማካሄድ የጀመረው።

በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የክልሉ መንግስት የ2011 በጀት ዓመት የመንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ሲሆን ውይይት የሚደረግበት ይሆናል።

ምክር ቤቱ በቆይታው የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን፥ የ2012 አጠቃላይ በጀት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በዛሬው እለት መካሄድ የጀመረው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እስከ ሐምሌ 25 2011 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።