ለኢትዮጵያና ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመታሰቢያ ስነ ስርአት በቤተመንግስት ተከናወነ

በብሄራዊ ቤተመንገስት ውስጥ በሚገኘውና በዋነኝነት በጃፓን መንግስት በልዩ ሁኔታ ጥበቃ በሚደረግልት የአትክልት ስፍራ የኢትዮጵያና ጃፓንን ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ለማስታወስ የሻይ ማፍላት ስነስርአት ተከናወነ፡፡

ይህ የአትክል ቦታ በአሁኑ ጊዜ በጃፓን መንግስት ልዩ ጥበቃ እየተደረገለት የሁለቱን ሀገራት ባህልና ትስስር በሚያሳይ ይዞታ ላይ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ 1956 ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በጃፓን ያደረጉት ጉብኝት ተከትሎ ከአመታት በኋላ የጃፓና ልኡል አዲስ ካገባት ባለቤቱ ጋር በመሆን የጫጉላ ሽርሽራቸውን በአዲስ አበባ በማድረግ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ህዝብ ለህዝብ ቀረቤታ አሳድገውታል፡፡

በወቅቱ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ሁለቱን ሙሽሮች ተቀብለው ከማስተናገድ ባሻገር በብሄራዊ ቤተመንገስት ለጃፓን ህዝብ መታሰቢያ የሚሆን የአትክልት ቦታ በመስጠት ቋሚ ማስታወሻ አስቀምጠዋል፡፡

በተለይም ቀዳማዊ ሀይለስላሴ እ.ኤ.አ 1956 በጃፓን ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ለሁለቱ ሀገራት አዲስ የግንኙነት ምእራፍ በመክፈት ግንኙነቱም ወደ ህዝብ ለህዝብና የባህል ቅርርብ እንዲያመራ አድርጎታል፡፡

ይህ የንጉሱ የጃፓን ጉብኝት በወቅቱ በሁለተኛው አለም ጦርነት ተሸናፊ ለሆነችው ጃፓን  ከነበረችበት መገለል በማውጣት ዲፕማሲያዊ መነቃቃት የፈጠረላት በመ፣ሆኑ አጋጣሚው በጃፓኖች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ አለው፡፡

የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት በመዘከር የዲፕሎማሲ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ በሚገኘው በዚህ የአትክልት ስፍራ የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎችና  አምባሳደሮች በተገኙበት የጃፓን የሻይ ማፍላት ስነ ስርአት ተካሂዷል፡፡ይህ ስነስርአት የኢትዮጵያ እና የጃፓንን የዘማናት ወዳጅነት በማስታወስ ግንኙነቱን ለማደስ የሚያስችል መነቃቃት ለመፍጠር የሚያግዝ ስለመሆኑ ተገልጧል፡፡

ጃፓን  ለኢትዮጵያ ንካራ የልማት አጋር ስትሆን በተለይም በትምህርት እና ስልጠና ዘረፍ የሰው ሀይል ልማት ላይ ከፍተኛ እገዛ እያደረገች ትገኛለች፡፡

የከፍተኛ ትምህረት ሚኔስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ትምህርተቻወን በጃፓን  የተከታተሉ ሲሆን  ከጃፓን ማህበረሰብ ጋርም ጠንካራ ቀረቤታ አላቸው፡፡

ጃፓኖች ከኢትዮጵያ ጋር የሚያመሳስላቸው በርካታ ጎዳዮች እንዳሉ የሚጠቅሱት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ያም ሆኖ ኢትዮጵያውያን ከጃፓኖች ልንማራቸው የሚገቡ የእድገት እና የባህል መሰረቶች መኖራቸውን ያነሳሉ፡፡

በብሄራዊ ቤተ መንገስት በሚገነው የጃፓን የአትክልት ስፍራ በተካሄደው  መርህ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ቡና እና የጃፓን ሻይ ማፍላት ስነ ስርአት ተካሂዷል፡፡ሁለቱ ሀገራት ከሻይና ቡና ስነስረአት  ባሻገር በተለያዩ ባህሎች የሚያመሳስላቸው እሴት ያላቸው ሀገራት በመሆናቸው አጋጣሚው የባህል መቀራረቡን ወደ ህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማሳግ መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተገልቷል፡፡

የኢትዮጵያና የጃፓን ግንኙነት እ.ኤ.አ ከ1930ቹ ጀምሮ በተለያዩ የእድገት ምእራፎች ውስጥ ያለፈ ቢሆነም ይህ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ወደ ላቀ የዲፕሎማሲ ግንኙት ምእራፍ የተሸጋረው ግን 1950ዎቹ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡