ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኳታር ምክትል ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያዩ

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኳታር ምክትል ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራሕማን ቢን ጃሲም አል ታኒ ጋር ተወያዩ፡፡

ሁለቱ ወገኖች ጠ/ሚሩ በመጋቢት ወር 2011 በኳታር ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተጀምረውን ውይይት በማስቀጠል በቁልፍ የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡

ሼክ መሐመድ ከዚህ ቀደም ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በሆቴል፣ ስኳር ፋብሪካ፣ በቱሪዝም ልማትና አዳዲስ የኩላሊት ሕክምና ማዕከላት ግንባታን ለማስጀመር ዝግጁነት እንዳለ መግለጻቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።