ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ጋር ተወያዩ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ጋር ተወያዩ፡፡

ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማሳደግ በትምህርት፣ የመካከለኛ አመራር ደረጃን የማሳደግ ስልጠና እና የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም በማጎልበት ረገድ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ፕሬዝዳንቷ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ዘርፈ ብዙ መሆኑን አንስተው ይህንን ለማጠናከር በትምህርት፣ በጤና እና በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ሀገራቸው ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም መረጋገጥ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀው በተለይ በቅርቡ በሱዳን መረጋጋትና በሰላማዊ የስልጣን ክፍፍሉ ላይ የነበራትን ሚና ልዩ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ነው፡፡