ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማና ልዑካቸው ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴዎች በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት አድረገዋል፡፡

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገር በቀል ሪፎርምን አድንቀው፣ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንግሊዝ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

(ምንጭ:-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)