የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ካውንስል አባላት ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የካውንስል አባላት ጋር በትናንትናው እለት ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባደረጉት ንግግር፥ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ በሌሎች ሀገራት ተሰርቶበት ለገፅታ ግንባታና ለመልካም ወዳጅነት በጎ ሚና መጫወቱን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ካለው አቅም ጋር ሲነፃፀር ግን ቨፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዘፍር ብዙ እንዳልተሰራ ያመላክተዋል ሲሉም ተናግረዋል።

ስለሆነም ያለውን አቅም በተሻለ ለመጠቀም ቀደም ብሎ በነበረው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ላይ አዳዲስ አባላት በመጨመርና መመሪያ በማዘጋጀት እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ተቃማትን በማስፋት ለአዲስ የዲፕሎማሲ ስራ ዝግጅቶች መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ካውንስል አባላቱ በበኩላቸው መመርያው ላይ ቢሻሻል የበለጠ ውጤት ያመጣል ያሉትን እንዲካተቱ ሃሳበ አቅርበዋል።

ከበፊቱ የላቀ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚችሉ ለዚህም ተግባር በመመረጣቸው ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን 75 አባላትን ያቀፈ ሲሆን፥ ከታዋቂ ሰዎች፣ ከሀይማኖት አባቶችና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለስቦችን በማካተት ከስምንት አመት በፊት መዋቀሩ ይታወቃል።