ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ኮሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ጃፓን አቀኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ኮሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ጃፓን አቅንተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ42 አገራት መሪዎች በሚሳተፉበት የቲካድ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነው ወደ ጃፓን ያቀኑት፡፡

በዮኮሃማ ጃፓን ለሶስት ቀናት ለሚካሄደው የቲካድ የመሪዎች ስብሰባ በሚኒስትሮች ደረጃ የሚመክረው የአፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል ፡፡

በአፍሪካ ልማት ዙሪያ ምክክር የሚያደርገው የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ/ ቲካድ/ እ.አ.አ ከ1993 ጀምሮ አፍሪካ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ በጃፓን ጠንሳሽነትና አመራርነት የሚካሄድ ነው።

በጥምር አዘጋጅነትም የአለም ባንክ፣ የተመድ ልማት ድርጅት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እየተሳተፉ ይገኛል፡፡