ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኮይካ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኮይካ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኮርያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ፕሬዝዳንት ጋር ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ የበለጠ በሚጠናከርበት ዙሪያ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮይካ በኢትዮጵያ በተለይም በትምህርት፣ በውሃና ግብርና ዘርፎች ላይ የሚያደርገውን የልማት ድጋፍ አድንቀዋል።

ኮይካ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ኃላፊዎቹ መገግለፀፃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡