ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሄስያን የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓውያኑ የ2019 የሄስያን የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን በጀርመን የፍራንክፈርት ከተማ የሚገኘው የፍራንክፈርት የሰላም ጥናት ማዕከል ገለጸ፡፡

የጥናት ማዕከሉ እንዳስነበበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ታሪካዊውን የሰላም ስምምነት መፈጸም በመቻላቸው የሄስያን የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆን ችለዋል ብሏል።

ሽልማቱም መስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚበረከትላቸው የፍራንክፈርት የሰላም ጥናት ማዕከል አሳውቋል።

ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአፍሪካ ተስፋ ከሚጣልባቸው መሪዎች አንዱ መሆናቸውንም ተቋሙ ገልጿል፡፡

የፍራንክፈርት የሰላም ጥናት ማዕከል በቀድሞው የሔሰን ግዛት ጠቅላይ ምኒስትር አልበርት ኦስዋልድ የተመሰረተ ሲሆን፣ ላለፉት 26 አመታት ለዓለም አቀፍ መግባባት እና ሰላም የላቀ ሚና ላበረከቱ ግለሰቦች ሽልማት ሲያበረክት ቆይቷል።