የደቡብ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን መካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በቆይታው የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪምም የክልሉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤትን ሪፖርትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።

በሌላ በኩል የምክር ቤቱ አባላት ከመደበኛ ጉባኤው አስቀድሞ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በሀዋሳ ከተማ መክረዋል።

ምክክሩ በሀገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታና ክልላዊ ጉዳዮች ምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚለውንና በክልሉ እየተነሱ ያሉት የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በሚመለከት የተደረገ እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡