የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ።

የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ ጉባኤው ነው አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር በማድረግ ነው የሾመው።

ምክትል ርእሰ መስተዳደር ተደርገው የተሾሙት አቶ ርስቱ ይርዳውም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

አቶ ርስቱ ከዚህ ቀደም ከወረዳ ጀምሮ ከጉራጌ ዞን አስተዳዳሪነት እንዲሁም በፌደራል የኃላፊነት ቦታዎች ሰርተዋል።

ዛሬ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሆነው እስከሚሾሙ ድረስም አቶ ርስቱ ይርዳው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን በማገልገል ነበሩ። (ኤፍ ቢ ሲ)