ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እስራኤል ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እስራኤል ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬም በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ ፅህፈት ቤት የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በእስራኤል የሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይህ ይፋዊ ስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል እና ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም በመጎብት ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ፣ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬቬን ሪቭሊን ጋር ይወያያሉ ተብሏል፡፡

እንዲሁም በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳዊያን ማስታወሻ ሀውልትን እና የሀገሪቱን የሳይበር ዳይሬክቶሬት እንደሚጎበኙ ነው የሚጠበቀው፡፡

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርና፣ በውሃና መስኖ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ዘርፎች ላይ በትብብር ይሰራሉ፡፡

በፀጥታ፣ ግብርና እና በቴክኖሎጂ በተለይ በሳይበር ዘርፍ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በእስራኤል የሚያደርጉት ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ለማጠናከር ሀገራቱ ያላቸውን ፍላጎት ማሳያ መሆኑንም በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ አስታውቋል፡፡