ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በተለያዩ የውጭ ሃገራት የነበራቸውን ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና እስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በደቡብ ኮሪያ ቆይታቸው ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር እንዲሁም ከሀገሪቱ የተለያዩ ኩባንያ  ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር ውይይት ካካሄዱ በኋላም ሁለቱ ሀገራት የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራመዋል።

በተመሳሳይ በጃፓን እና እስራኤል ቆይታ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተለያዩ ስምምነቶችን ማድረጋቸው  የሚታወስ ነው፡፡