ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የፍትህ ቀን ይከበራል

ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የፍትህ ቀን “መደመር ለፍትህ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ “የህግ ተገዢ ነኝ!” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የቆየው የፍትህ ወር ማጠናቀቂያ ዝግጅትም በዛሬው ዕለት ይካሄዳልም ተብሏል።

ፍትህን ማረጋገጥ ለነገ ይደር የማይባል ስራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ድረገፁ አስታውሷል፡፡

ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከ15 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ዝግጅት ከቀኑ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከናወናል፡፡

የዘንድሮ ጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶችና ርዕሰ ጉዳዮች እየተከበሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡