ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የዲሞክራሲ ሽልማትን አሸነፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የአፍሪካ ዴሞክራሲ ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ለሽልማቱ የበቁት ዴሞክራሲን እና መልካም አስተዳደርን በአፍሪካ ለማረጋገጥ ባደረጉት ጥረት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሽልማቱ በአዲስ አበባ በተካሄደው በአራተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ የምክክር መድረክ ላይ ነው የተበረከተላቸው፡፡

ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪዎች የሽልማቱ አዘጋጆች መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል፡፡

የአዘጋጅ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ኪንዴ ባሚግበታን ሽልማቱ በአህጉሪቱ ዴሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን በማስፋፋት ተምሳሌታዊ ተግባር ላከናወኑ ሰዎች እውቅናን የሚቸርና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በተጨማሪ ናይጄሪያዊው ቦላ ቲኒቡ የዚህ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ምንጭ ፦ፖለቲክስ ናይጄሪያ