ጠ/ሚ ዐቢይ ሆሳዕና ከተማ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ገብተዋል፡፡  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ በሚኖራቸው ቆይታ ከዞኑ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በከተማዋ ስታዲየም ለተሰበሰበው ህዝብም ንግግር እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ጠቁሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ባለፈው ሳምንት ከካፋ ዞን ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡