አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ለውጥ አደነቁ

ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ኒውዮርክ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ዋና ፀሃፊው በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ለውጥ በእድናቆት እንደሚመለከቱት በዚህን ወቅት አንስተዋል፡፡

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ በሱዳን ድርድር ላይ ያሳደረችውን ተፅእኖ በማድነቅ በደቡብ ሱዳንም ተመሳሳይ ስራ እንድትሰራ ጠይቀዋል፡፡

ከኒዉዮርኩ ጉባኤ ጎን ለጎን የኘሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ሜርክል በመሩትና በአፍሪካ የሰላምና፣የደህንነትና የልማት ጉዳይ ላይ በተነጋገረዉ የምክክር መድረክ ላይ ተሳትፈዋል ።

ውይይቱ በዋናነት በሰላም፣ ደህንነትና የልማት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።