ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፊንላንዱ ፕሬዚደንት ሳውሊ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፊንላንዱ ፕሬዚደንት ሳውሊ ኒሲቶ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ሽልማቱ 10 በመቶ እውቅና፣ 90 በመቶ ደግሞ ለሰላም በርትተው እንዲሠሩ አደራም ጭምር እንደ ሆነ ጠቁመው ለውጡ ያስገኛቸውን ዋና ዋና ስኬቶች እንዲሁም የፊንላንድ መንግሥት ድጋፍ ሊያደርግባቸው የሚችልባቸውን የልማት አቅጣጫዎች አመላክተዋል።

ሁለቱ መሪዎች የጋራ ጥቅምን እውን በሚያደርግ መልኩ የአፍሪካና የአውሮፓን ግንኙነት በማጠናከር ሂደት ላይ መምከራውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡