የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ስጦታ አበረከቱ

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ሽልማት አበርክተውላቸዋል፡፡

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ስጦታውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አበርክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆናቸውን አባላቱ መደሰታቸውን የገለፁት አቶ ለማ ፤ ሽልማቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል የተሰጠ እውዕና መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተያየዘ ዜና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው የክልሉ መንግስት የስራ አፈፃፀምን በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በለውጥ ጉዞ ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ በመምከር የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኦሮሚያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡