የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ዛሬ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ ፓርቲና እንደ መንግስት ያለውን አፈጻጸም በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

የፓርቲው የውስጥ አንድነትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፎርም ጉዳይም የውይይቱ አጀንዳ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ለአገራዊ ለውጡ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች ተለይተው የመፍትሔ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ከኦሮሚያ  ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።