የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ይጀምራል

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማካሄድ ይጀመራል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድም ነው የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኝነት እና የኮንፈረንስ አገልግሎት ፅህፈት ቤት ያስታወቀው፡፡

የፅህፈት ቤቱ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ታረቀኝ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ በሦስት የቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም በጀት፣ የስራ አስፈፃሚ፣ የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የዋና ኦዲተር የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ረቂቅ እድቅ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ የዳኝነት የአገልግሎት ክፍያ፣ የዳኞች ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ተሻሽሎው የወጡ ረቂቅ አዋጆች እና ሌሎች አዋጆችን ጨምሮ 5 የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ ከተወያየ በኋላ እንደሚያፀድቅ አቶ ሙሉጌታ ታረቀኝ አክለው ገልፀዋል፡፡