የኢትዮጵያን ህዳሴ ዕውን ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው-ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም

አዲስ አበባ ሐምሌ 26/2008 (ዋኢማ) የኢትዮጵያን ህዳሴ እውን ለማድረግ ግዜው አሁን መሆኑን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም አስገነዘቡ ፡፡

ዶክተር ቴድሮስ ትናንት በባህርዳር ከተማ የተጀመረው  የዲያስፖራ ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር በሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው 10 ነጥብ 8 አማካይ ኢኮኖሚ ዕድገት ህዳሴዋ ዕውን እንደሚሆን ማረጋገጫ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

በመላ አገሪቱ በጤና ፣ትምህርት፣በመንገድና በስራ ዕድል ፈጠራና እንደዚሁም ሰላምና መረጋጋት ከማረጋገጥ አንጻር የተገኙ አበረታች ውጤቶች አብራርተዋል ፡፡

የዲያስፖራው አባላት የአገራቸው አምባሳደር በመሆን በዕውቀት ፣በሳይንሰና ቴክኖሎጂና መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ የአገሪቱን ህዳሴ ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ርቦርቦሽ ላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ፡፡

አያይዘውም የአገሪቱ ዕድገት ማጉላት በአገሪቱ ያሉ ችግሮች ማካካሻ ሊሆን አይገባም ሲሉ አስገንዝበዋል ፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ዕድገት አደጋ የሆነው የመልካም አስተዳደር እጦትና ሙስና ለማዳከም በሚደረገው ጥረት ዲያስፖራው የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል ፡፡

የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከዳያስፖራ አባላት በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ፓናል ላይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣ የጉሙሩክ ስርዓትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ፣የዳያሰፖራ የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ አከፋፈት እና የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶችና ፕሮግራም በሚሉ  ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል ፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ዳያስፖራ ቀን በዓል መዝጊያ ላይ 10ነጥብ በ6 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 157 ዳያስፖራዎች ዕውቅናና ሽልማት በመስጠት መጠናቀቁን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ፡፡