በክልሉ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ንግድ ላይ የተሰማሩ ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 26/2008(ዋኢማ)-በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በእስራትና ገንዘብ መቀጣታቸውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ ፡፡

ፍርድ ቤቱ ለዋልታ እንዳስታወቀው ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ሰዎችን ወደ ውጭ በመላክ ህገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማራው ሁሴን መሀመድ ፈንታሁን በ25 ዓመት ፅኑ እስራትና 10 ሺ ብር ተቀጥቷል፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ ሁሴን የፈፀመው ህገ ወጥ ድርጊት በማስረጃና ምስክሮች መረጋገጡን ፍርድቤቱ ጠቁሟል ፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያረዳው ተከሳሹ በተለያዩ ጊዜያት 46 ሰዎችን ‹‹ወደ ሳዑዲ አረቢያ በባህር እልካችኋለሁ›› በማለት ህገ ወጥ ድርጊት መፈጸሙንና ከ17 ሰዎች ላይ ብቻ 84ሺ ብር መቀበሉ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡

ገንዘብ የተቀበላቸው ሰዎች በየበረሃው እየወደቁ ለረሀብና እንግልት መዳረጋቸው በክስ መዝገቡ ተመልክቷል፡፡

ጅቡቲ ድረስ ወስዶ የጣላቸውና ለሌሎች ደላሎች ያስረከባቸው የግል ተበዳዮች መኖራቸውም ፍርድቤቱ ገልጿል፡፡

ከጅቡቲ በጀልባ ወደ የመን የላካቸው ተበዳዮችም ለከፍተኛ ስቃይ ተዳርገዋል ይላል ፡፡ 

ተከሳሹ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል መፈጸሙ ምርመራው በፖሊስ ተጣርቶ ክሱ በሰሜን ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ አማካኝነት ለሰሜን ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም ክሱንና ማስረጃውን አጣርቶ ሰኔ 03 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡

በተያያዘ ዜናም በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ በቆቦ ከተማ ህገወጥ ንግድ ሲያካሂድ የተገኘ ግለሰብ በገንዘብና እስራት መቀጣቱን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዋቢ አድርጎ ለዋልታ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ተከሳሽ ካሳ ተፈራ ገሰሰ የነዳጅ ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው በቆቦ ከተማ 04 ቀበሌ ልዩ ቦታው አምቡሌ በሚባለው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የናፍጣ ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ሲሸጥ በመገኘቱ በ8 ዓመት ፅኑ እስራትና በ25ሺ ብር እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡

ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ በተከሳሽ መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻ በናፍጣ የተሞሉ 11 ባለ 25 ሊትር ጀሪካኖች፣ ግማሽ በርሜል ናፍጣና ባለ 25 ሊትር 21 ባዶ ጀሪካኖችን አግኝቷል፡፡