የ133 ኪሎሜትር እርዝመት ያለው የኮምቦልቻ-ባቲ-ሚሌ የአስፋልት መንገድ የግንባታ ሥራ ከ82 በላይ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ ።
የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለዋልታ እንደገለጹት በጠጠር ደረጃ የነበረው የኮምቦልቻ-ባቲ-ሚሌ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ግንባታው እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል ።
የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ በአማራና በአፋር ክልል መካከል ያለውን የትራፊክ ፍሰትና የአካባቢውን ህብረተሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳድግ መሆኑን አቶ ሳምሶን አክለው ገልጸዋል ።
የመንገድ ፕሮጀክቱ በሁለት ኮንትራት ተከፋፍሎ ግንባታው እየተከናወነ ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው የኮምቦልቻ-ቡርቃ የ60 ኪሎሜትር መንገድ ዦንግሜይ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተባለ የቻይና ዓለም ዓቀፍ የሥራ ተቋራጭ ድርጅት ግንባታው እየተካሄደ እንደሚገኝ አቶ ሳምሶን አመልክተዋል ።
እንደ አቶ ሳምሶን ገለጻ የፕሮጀክቱ የሁለተኛው ኮንትራት ግንባታ 73 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን ሻንግሃይዌይ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ግሩፕ የተባለው የቻይና ዓለም አቀፍ የሥራ ተቋራጭ ድርጅት እየተገነባ ይገኛል ።
የኮምቦልቻ-ባቲ-ሚሌ የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድርና ከኢትዮጵያ መንግሥት በተመደበ በአጠቃላይ በ2ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ።
የ133 ኪሎሜትር እርዝመት ያለው የኮምቦልቻ-ባቲ ሚሊ የአስፋልት መንገድ የግንባታ ሥራ ከ82 በላይ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ ።