ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ ዓመት በተማሪዎች ኢንፈርሜሽን ማኔጅመንት ዘዴ አማካይነት ለተማሪዎቹ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕረዚዳንት ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለጹት፤ የዩኒቨርሲቲው ለመስጠት የተዘጋጀው ፈጣን አገልግሎት የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ምርቃት ያለውን ወረቀት አልባ የሚያደርግ ነው::

ተማሪዎች የሚመረቁት የመማር ማስተማር ሂደቱ ከምዝገባ እስከ ምረቃ ድረስ በርካታ ሂደቶችን አልፈው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ስለሆነም  የተጠናና የተደራጀ ሰርዓተ ትምህርት ያስፈልጋል ብለዋል ።

በአዲሱ ዓመት የሚቀበሉዋቸው ከ6ሺ በላይ ተማሪዎች ባሉበት መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል ፡፡።

አጠቃላይ ተማሪው በአዲሱ ዓመት በአንድ ካርድ ዜዴ እንደሚጠቀሙ ፕረዚዳንቱ አስታውቀዋል  ፡፡

በዚሁም መሰረት ተማሪው አንድ መታወቂያ ይዞ ቤተመጻሕፍት መግባት ይችላል ብለዋል ።

እንደዚሁም ተማሪዎች ምግቤት ሄደው ተጠቃሚ መሆን ያለመሆናቸውን በቀላሉ ማወቅ እንደሚችሉ አስረድተዋል ።

በካርዱ በመገቢያ በር ላይ መግባት ይችላሉም ብለዋል ።

የተማሪዎች ውጤት በሞባይላቸው መረጃ ይላክላቸዋል ያሉት ዶክተር ደሳለኝ ፤ በኢንተርኔት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉም አመልክተዋል ፡፡

እንደዚሁም መምህሩ ፈተና የሚያስገባበት ቀነ ገደብ እንደተቀመጠለትና በነዛ ቀናት ካላስገባ ሶፍትወሩ እንደማያስገባም አስታውቀዋል  ።

በዚሁም መሰረት የዩኒቨርሲቲው መምህራን በተሰሰጣቸው ጊዜ ተካታታይ ምዘና ይሰጣሉ ብለዋል  ።

ዩኒቨርሲቲው ድህረ ምርቃ ጨምሮ በመደበኛ ፣በተከታታይና በክረምት 32 ሺ እያስተናገደ መሆኑ ይታወቃል ፡፡