የ2009 ዓም የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም፣ በደስታና በድምቀት እየተከበረ መዋሉን የተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ ።
ዋኢማ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የተለያዩ የአዲስ አበበ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት የ2009 የአዲስ ዘመንን በሰላም ፣ በደስታና በፍቅር ማክበራቸውን ።
አዲሱ ዘመን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ፣ የሰላም፣ የፍቅርና የመከባባር እንዲሆንለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።
በከተማዋ የካራ ቆሬ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ወይሳ ጥርአይሎ እንደገለጹት ከዋዜማው አንስቶ የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓሉን ለማክበር ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውንና በሰላም ማክበራቸውን ገልጸው አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ የሰላም ፣ የደስታና የዕድገት እንዲሆን ተመኝተዋል።
ወጣት ዳናዊት ለምለም በበኩሏ አዲሱን ዓመት ካለፉት ዓመታት በህይወቷ ላይ የተሻለ ለውጥ በማምጣት የምትጥርበት መሆኑን ጠቁሟ ወጣቶች እራሳቸውን በመለወጥ ለአገር ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበት ዘመን እንዲሆን ተመኝታለች ።
በአዲስ አበባ ከተማ የኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ ነዋሪ የሆነው ከበደ እሸቱ የዘንድሮ የአዲስ ዓመት በዓል በአዲስ መንፈስ እንደተቀበለው በመግለጽ ሁሉም ዜጋ በአዲሱ ዓመት ለሰላም ፣ ለዴሞክራሲና ለልማት የሚቆምበት እንዲሆን ተመኝቷል ።
ሌላዋ የአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነቺው ዓለም ተሰማ አዲሱን ዓመት የምትቀበለው ከባለፉት ዓመታት በተሻለ መልኩ ኑሮዋን የማሻሻል የያዘችውን ዕቅድ ለማሳካት ከልብ በመነሳት ነው ብላለች ።