የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

በዓሉ በሚከበርበት ሆራ አርሰዲ ሃይቅ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ የበዓሉ አክባሪዎች በመገኘት የክብረ በዓሉን ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል ።

በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ላይ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተሳታፊዎችና ጎብኝዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ገዳ ስርዓት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ፡፡
የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ሲተዳደርበት የነበረው የገዳ ስርዓት የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከማጠናከሩም ባሻገር የመከባበር ባህል እንዲጎለብትና ህብረተሰቡ በሁለንተናዊ መልኩ መለወጥ እንዲችል መሰረት የሆነ ስርዓት መሆኑ ተመልክቷል ፡፡
የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ ትናንት በቢሾፍቱ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በፓናል ውይይቱ የገዳ ስርዓትን በተመለከተና የገዳ ስርዓትን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርትና ባህል ተቋም/ዩኔስኮ/ ለማስዝገብ እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚመለከት የመወያያ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የገዳ ስርዓትን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተደረገ ያለው ጥረት በስኬት እንዲጠናቀቅ ህዝቡ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት በውይይት ላይ ተካፋይ የነበሩ አባገዳዎች ገልጸዋል ፡፡

አባገዳዎቹ አይይዘውም የኢሬቻ በዓል ከየትኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ ነጻ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡
በውይይቱ በየስምንት ዓመት የጊዜ ገደብ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ያለው የገዳ ስርዓት ለሰላም መስፈንና ለሴቶች መብት እንዲሁም ለተፈጥሮ ሃብት ክብካቤና ለትምህርት ልዩ ስፍራ ያለው የኦሮሞ ህዝብ የአስተዳደር ስርዓት መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በ2003 በተደረሰው በማይዳሰሱ ቅርሶች ስምምነት መሰረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርትና ባህል ተቋም /ዩኔስኮ/ ሀገራችን እስከአሁን የመስቀል በዓልና የፊቼ ጨምበላላ በዓልን ያስመዘገበች ሲሆን የገዳ ስርዓት በውስጡ ባቀፋቸው ዴሞክራሲያዊና ባህላዊ እሴቶች የተነሳ በመጪው ህዳር ወር የማይደሰስ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ዘርፍ ሆኖ በዩኔስኮ ይመዘገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሀገራችን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በሂደት ላይ ካሉ ሌሎች ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አምስት ቅርሶች መካከል አራቱ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይገኛሉ ዋልታ እንደዘገበው ፡፡