በሀገራችን ከ5 ሚሊየን በላይ ህዝብ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆነ

በሀገራችን 5ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተጠቃሚ መሆናቸውን የውሃ ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
 

ባሳለፍነው ዓመት በገጠር 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በከተማ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በድምር 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ ገልጸዋል ፡፡

በዚህም መሰረት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን የገጠር እና 0 ነጥብ 7 ሚሊዮን የከተማ በድምር 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች በተሻሻለው የአገልግሎት መሠረት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት  ተጠቃሚ መሆናቸውን  አስታውቀዋል ፡፡
 

በመሆኑም በገጠር የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በአዲሱ መስፈርት በገጠር 63 ነጥብ 1 በመቶ በከተማ 52 ነጥብ 5 በመቶ አገራዊ 61 በመቶ ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል ፡፡

ህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታቸው እንዲሻሻልና ለውሃ ፍለጋ ያጠፉት የነበረውን ጊዜ ለልማት ማዋል ያስቻላቸው ሲሆን ፤ውሃን ለማጓጓዝ ያወጡት የነበረውንም ወጭያቸውን እየቀነሰላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በአዲሱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት መስፈርት በገጠር በቀን ለአንድ ሰው 25 ሊትር በአንድ ኪሎ ሜትር ውስጥ እና በከተማ እንደየከተሞቹ ደረጃ ከ40 ሊትር እስከ 100 ሊትር  በቀን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

 

በ20012 ዓም በገጠር የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋኑን 85 በመቶ ማድረስና 20በመቶ የቧንቧ ተጠቃሚ ማድረግና በከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋኑን 75 በመቶ ማድረስና ሁሉም የቧንቧ ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን አመልክተዋል ሲል ዋልታ ዘግቧል ፡፡