ኢንተርፕራይዙ ከ18 ሺህ በላይ 40/60 ቤቶች ግንባታ 55 በመቶ መድረሱን አስታወቀ

በ40/60 የቤት ልማት መርሃግብር ከ18 ሺህ በላይ ቤቶች ግንባታቸው ከ55 በመቶ በላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ አስታወቀ።

በሶስት ምዕራፍ በተከፈለው የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም  ከ39 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከሚገነቡት ውስጥ ከ18ሺ 500 ቤቶች ግንባታቸው በመፋጠን ላይ መሆኑን የኢንተርፕራይዙ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ አባይነህ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል አስታውቀዋል፡፡

እነዚህ በሁለተኛው የግንባታ ምዕራፍ የሚገነቡት ቤቶች በአማካኝ ከ55 በመቶ ወይም ከ9ኛ ፎቅ በላይ መድረሳቸውን ነው የገለጹት ፡፡

ከነዚሁም ውስጥ ደግሞ በመጀመሪያው ምዕራፍ በሰንጋተራና ክራውን ሳይት የተገነቡት 1 ሺህ 292 ቤቶች ከተወሰኑ ጥቃቅን የለቀማ ስራዎች በስተቀር አጠቃላይ የግንባታ ስራው መጠናቀቁን ነው ያስረዱት ፡፡

እነዚህ ቤቶች  ተሎ ባለመተላለፋቸው  በተጠቃሚዎች ዘንድ የሚሰማውን እሮሮ ምላሽ ለመስጠት ምን ታስቧል ? ለሚለው ጥያቄም አቶ ዮሃንስ ሲመልሱ “ መንግስት  ቀኑን ሲወስን ይተላለፋሉ” ብለዋል  ፡፡

በሶስተኛው ምዕራፍ ከ19 ሺህ በላይ ቤቶች  በአማካኝ የግንባታ አፈፃፀማቸው 25 በመቶ  መሆኑን አመልክተዋል ፡፡

ከባለ 8 ወለል እስከ እስከ ባለ 18 ወለል ከፍታ ያላቸው 371 ህንፃዎች ግንባታ በ13 የግንባታ ሳይቶች እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

ከመሰረተ ልማት ዝርጋታና ከግብዓት አቅርቦት እጥረት ጋር በተያያዘ ችግሮች በማጋጠማቸው በእነዚሁ ሳይቶች የተገነቡት 1 ሺህ 292 ቤቶች ግንባታቸው መጋተቱንም አልሸሸጉም ፡፡

በሌሎች ሳይቶች የሚካሄዱ ግንባታዎች ግን በተያዘላቸው የጊዜ እቅድ መሰረት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

ኢንተርፕራይዙ በየዓመቱ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አዳዲስ የስራ እድሎችን መፍጠሩን አቶ ዮሃንስ አስታውቀዋል ፡፡

በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ከ500 በላይ ማህበራት በ2008 በጀት አመት ብቻ ከ208 ሚሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር እንደተፈጠረላቸው ገልጸል፡፡      

በግንባታ ስራው ላይ ከደረጃ አንድ እስከ ሶስት የሚገኙ 151 የስራ ተቋራጮች እና ዘጠኝ ደረጃ አንድ አማካሪ ድርጅቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ነው ያሉት ፡፡

የአቅም ውስንነት የተስተዋለባቸው የግንባታ ተቋራጮችም ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ ውል እስከማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስታውቀዋል ።

በሳሙኤል ዳኛቸው