የፈጣን አውቶቢስ አገልግሎቱ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ያቃልላል ተባለ

የአዲስ አበባ አበባ  ፈጣን የአብቶቢስ ትራንስፖርት አገልገሎት  በአገልግሎት ላይ  ከሚገኘው  የአዲስ አበባ  ቀላል  የባቡር  አገልግሎት  በመቀጠል  የአዲስ አበባ ከተማን  የትራንስፖርት  ችግር  ያቃልላል ተባለ ። 

የአዲስ አበባ  ፈጣን የአውቶቢስ ትራንስፖርት  አገልገሎት  ከሶስት ዓመታት በፊት ዲዛይኑ አልቆ   ወደ ሥራ  ወደ ትግበራ ምዕራፍ  የተሸጋገረ  ሲሆን  ግንባታው ሲጠናቀቅ  በአዲስ  አበባ ከተማ  በሰባት ያህል  መስመሮች አገልግሎት በመሥጠት  የከተማዋን  የትራንስፖርት ችግር ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል ። 

የፕሮጀክቱ  ጽህፈት  ቤት ኃላፊ የሆኑት  አቶ ልዑል ኃይሉ እንደሚናገሩት ከሰባቱ መስመሮች ውስጥ አንዱ  የሆነው ከ ውንጌት ተነስቶ  ጆሞ ላይ የሚጠናቀቀው መስመር  በአጠቃላይ  በ50  ዮሮ ግንባታው  እየተካሄደ ይገኛል ።  ለግንባታው   የሚውለውን  ገንዘብ  ከፈረንሳይ መንግሥት የተገኘ መሆኑንና    የከተማዋ ፖሊሲ   በሚያዘው መሰረት  የብዙሃን   ትራንስፖርትን  ከማሰፋፋት አኳያ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል ።     

እንደ አቶ ልዑል ገለጻ  አገልገሎቱ በከተማ  የሚታየውን  የትራፊክ መጨናናቅ  የሚያቃልል እንዲሁም በአንድ ቀን  በአንዱ  መስመር ብቻ  60ሺ በላይ   ሰዎችን ማጓጓዝ የሚያስችል  ነው ።

የቀሪዎቹ  የስድስት  መስመር ግንባታ የቅድሚያ ጥናት  ተጠናቀው  ለግንባታ ሥራው   አስፈላጊ  የሆነውን የገንዘብ ማፈላለግ ሥራ  እየተከናወነ መሆኑን   የሚናገሩት አቶ ልዑል    የአውቶቢሲቹ ሞዴል   በከተማዋ አገልገሎት  ከሚሠጡት  አውቶቢሶች የተሻለ እንደሚሆን  ገልጸዋል ።  

አጠቃለይ  ፕሮጀክቱ   ፋይናንስ የመፈለግና የጨረታ ሥራዎች  የሚቀሩት  በመሆኑ   እኤአ በ2018   ይጠናቀቃል  ተብሎ እንደሚጠበቅ   አቶ ልዑል ተናግረዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ  የተለያዩ   የብዙሃን  አማራጭ የትራንስፖርት  አገልገሎቶች የሆኑትን  እንደ ቀላል ባቡር ፣   የተለያዩ አውቶቢስ አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል ቢቻልም  አሁንም  የከተማዋ  የአብዙሃን የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት  በፍጥነት እያደገ መጥቷል ።