የድምፂ ወያነ ትግራይ መስራች ታጋይ ጎይተኦም ታደሰ አረፉ

የድምፂ ወያነ ትግራይ መስራች የነበሩት ጋዜጠኛና ታጋይ ጎይተኦም ታደሰ ዛሬ አረፉ፡፡ ጋዜጠኛና ታጋይ ጎተኦም ታደሰ ድምፂ ወያነ ትግራይ መስከረም 30/ 1972 ዓመተ ምህረት በኤርትራው “ድምፂ ሓፋሸ” ሬድዮ ውስጥ ፍቃድ አግኝቶ ሳሕል በተባለው ተራራ የሬድዮ ፕሮግራሙን ሲጀምር ከሶስት መስራች ታጋዮች አንዱ እንደነበሩ ሬድየው ገልጿል ፡፡

ደርግን ለመጣል እየተደረገ በነበረው መራራ ትግል ውስጥ ታጋይ ጎይትኦም ታደሰ  ሬድየው ስርጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለ37 ዓመታት በጋዜጠኝነትና በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ሲሰሩ የቆዩ ታታሪ እንደነበሩ ተመልክቷል ፡፡

ታጋይ ጐይትኦም ታደሰ ከአባታቸው አቶ ታደሰ ወ/ማርያም ከእናታቸው ወይዘሮ ግደይ ገብረዕቑባይ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በኣስገደ ጽምብላ ወረዳ በዓዲ ደጎል ቀበሌ መስከረም 7 /1945ዓመተ ምህረት ተወለዱ፡፡

ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ቀጥሎም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል  በመቐለ ከተማ መከታተላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል ፡፡

ታጋይ ጎይተኦም ታደሰ ደርግን ለመጣል በ1968 ዓመተ ምህረት ወደ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በመቀላቀል ጠንካራ ታጋይነታቸውን ያስመሰከሩ የህዝብ ልጅ እንደነበሩ ነው የተነገረው፡፡

ከደርግ ውድቀት በኋላ ደግሞ በመቐለ ቢዝነስ ኮሌጅ በዲፕሎማና ቀጥሎም በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ በማኔጅመንት ተመርቀው ስራቸውን በቅንነትና በትጋት ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ነው ዘገባው የገለጸው፡፡

ታጋይ ጎይተኦም ታደሰ በድምጺ ወያነ ትግራይ በቆዩባቸው በርካታ ዓመታት በጋዜጠኝነት፣ በማስተባበርና የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ በመሆን ማገልገላቸውን ሬድየው አስታውቋል ፡፡

ታጋይ ጎይተኦም ታደሰ ባደረባቸው ህመም በአገር ውስጥና በውጭ አገር በህክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ በ64 ዓመታቸው ህዳር 1/2009 ዓመተ ምህረት ረፋዱ ላይ አርፈዋል ፡፡

የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም ዛሬ ከቀኑ በ10 ሰዓት ላይ በመቐለ ከተማ በዓዲሽምድሑን እንዳማሪያም ቤተክርስትያን ይፈጸማል -(ድወት)፡፡