የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ ዛሬ ተከበረ ።
በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ዛሬ በተከበረው በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን እና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ተገኝቷል ።
እንደዚሁም በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምእመናንም የጥምቀት በዓሉ በድምቀት ሊከበር ችሏል ።
በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ ባህረ ጥምቀት በዓል ላይ የታደሙ የውጭ ዜጎች ለዋልታ በሰጡት አስተያየት አገሪቷ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ብትሆንም አስተማማኝ ሰላም ላይ እንደሚትገኝ መረዳት መቻላቸውን ገልጸዋል ፡፡
ጎብኚዎቹ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት የሰላም ስጋት እንደነበረባቸው ጠቁመመው፤ አሁን ግን የተለያዩ አከባቢዎችን በሰላም ጎብኝተው በበዓሉ መታደማቸው እንዳስደሰታቸው አስረድተዋል ፡፡
በዓሉ በዩኔስኮ እውቅና ሊያገኝ እንደሚገባም አስተያታቸውን ሰጥተዋል ፡፡
ከዚህ በፊት መጥተው የነበሩና ከዓመታት በኋላ አሁንም በድጋሚ በመጎብኘት ላይ የሚገኙ ቱሪስቶች በአገሪቱ በተለያዩ ዘርፎች የተመለከቷቸው ለውጦች አድንቀዋል ፡፡
ዓመታዊ የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሃንስ እጅ ለመጠመቅ ወደ በዮርዳንስ ወንዝ የወረደበትን ዕለት ለማሰብ የሚከበር መሆኑ ይታወቃል ።