በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ የሟቾች ቁጥር 46 ደረሰ

በአዲስ አበባ "ቆሼ" በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ የሟቾች ቁጥር 46  መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማዋ አስተዳደር ገለፀ፡፡

በአደጋው እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ የሟቾች ቁጥር 15 የነበረ ሲሆን እየተሰራ ባለው የህይወት አድን ስራ የሞቱት ቁጥር በሶስት እጥፍ ጨምሮ 46 መድረሱን አስተዳደሩ በተለይ ለኢቢሲ አመሻሽ ላይ ገልጿል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ በሚራው አካባቢ የቆሻሻ ክምር የመደርመስ አደጋ  የተከሰተው ትላንት ምሽት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ነበር፡፡

አደጋው በመኖሪያ ቤቶች ላይ የደረሰ በመሆኑ ለሰው ህይወትና ንበረት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡

ከአደጋው የተረፉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ሙሉ ንብረቶቻቸውና የሰው ህይወት ጉዳትና መጥፋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው እንዳሉት በአደጋው ህይወት መጥፏቱ አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው 37 ሰዎች በአለርት ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መካላከል ባለስልጣን እንዲሁም የከተማዋ ፖሊስ ምሽቱን በአደጋው ቦታ በመገኘት የሰው ህይወት ለማትረፍ ጥረት ሲያደርጉ ማደራቸውን ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ ድሪባ ኩማ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ተጎችዎችን ለማቋቋም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ሌሊቱን ሙሉ ሲካሄድ የነበረው አደጋው የመከላከል ስራ በአካባቢው ህብረተሰብ  ርብርብ ጭምር አሁም አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል፡፡ (EBC)