ሚኒስቴሩ የማንጎ በሽታን ለመቆጣጣር እየጣረ መሆኑን አስታወቀ

በአገሪቱ በሦስት ክልሎች  እየተዛመተ የመጣው ማንጎን የሚያጠቃውን  በሽታ ለመቆጣጣር  ጥረት  እያደረገ  መሆኑን የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት  ሚንስቴር አስታወቀ ።

በሚኒስቴሩ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት  አቶ አለማየሁ  ብርሃኑ ለዋልታ እንደገለጹት ከአሥር ዓመት በፊት  ከህንድ አገር ወደ ኢትዮጵያ  የገባውን የማንጎ በሽታን  በቁጥጥረ ሥር  ለማዋል እንቅስቃሴዎች  እየተካሄዱ ነው ።

በቅድሚያ  በወለጋ  የተከሰተው የማንጎ  በሽታ   በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እየተስፋፋ ይገኛል ብለዋል  ።

በተለይ  በነብሳት  አማካኝነት  የሚዛመተው የማንጎ በሽታ በቤኒሻንጉል  ክልል ሰፋ ያሉ የማንጎ ማሳዎችን  በማጥቃት ላይ እንደሆነ አያይዘው ገልጸዋል ።    

 የማንጎ በሽታን  ለመከላከል የፀረ-ተባይ መድሓኒት በእርሻ ቦታዎች ላይ  እየተረጨ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በነብሳት  አማካኝነት የሚሠራጨው  የማንጎ ባሽታ   ወደ ጎረቤት ክልሎች በስፋት  ተሠራጭቶ  ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል  የበሽታው ምንጭ የሆነውን  የነብሳት ሥርጭት ለመቆጣጣር ጥረት እየተካሄደ እንደሆነ አቶአለማየሁ አመልክተዋል ።