ህንጻዎች የአደጋ ጊዜ መውጫን በሟላ ሁኔታ ሊገነቡ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የሚገነቡ ህንጻዎች የአደጋ ጊዜ መውጫ  በሟላ ሁኔታ  ሊገነቡ  እንደሚገባ  ተገለጸ ።

በመላ አገሪቱ  የተለያዩ ከተሞች ትላልቅ ህንጻዎች እየተገነቡ ቢሆንም ለህንጻ  ተገልጋዮች የደህንነት ዋስትና የሆነው የአደጋ ጊዜ መውጫ በግንባታ ወቅት ስለማይሠራ አደጋ በሚከሰትበት ወቅት የሚደርሰው ጉዳት እያደገ መጥቷል ።

በተለይ  በከተሞች በህንጻዎችና በመኖሪያ መንደሮች ላይ የሚደርሰው የእሳት አደጋ  ከጊዜ  ወደ ጊዜ  እየከፋና  ችግሩም እያደገ  በመምጣቱ   በከተሞች  በሚገኙ  የተቋማትና የመኖሪያ ቤት ህንጻዎችን ላይ  የአደጋ  ጊዜ  መውጫ እጅግ  አስፈላጊነት እየሆኑ መምጣታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጣር ባለሥልጣን ባወጣው መረጃ መሠረት  በዘንድሮ በጀት ዓመት ስድስት ወራት ብቻ  በአዲስአበባ ከደረሱት 230  አደጋዎች ውስጥ  150 የሚሆኑት  የእሳት አደጋዎች መሆናቸው  ተመልክቷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ባለሥልጣን በበኩሉ  በዘንድሮ የበጀት ዓመት የአደጋ መውጫ በሌላቸው ህንጻዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ መግለጹን ዋልታ ሚዲያ ኮርፖሬት ዘግቧል ።