በአዲስ አበባ ከተማ 10ሺህ ለሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች በመንገድና ትራፊክ ደህንነት ላይ ሥልጠና እየተሠጠ መሆኑን የፌደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም ለዋሚኮ እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ በአጠቃላይ 10ሺህ ለሚሆኑ የታክሲና የሃይገር አሽከርካሪዎች ነው በመንገድና ትራፊክ ደህንነት ላይ የአንድ ቀን ሥልጠና እየተሠጠ ይገኛል ።
ሥልጠናው ከትናንትና ጀምሮ በተለያዩ አዳራሾች ከ4 ሰዓት እስከ 8 ድረስ በመንገድ አጠቃቀም ፣የአደጋ መከላከልና በማሽከርከር ብቃት ርዕሶች ላይ ሥልጠናው እንደሚያተኩር የጠቆሙት አቶ ካሳሁን የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎችን ስነምግባር ለማስተማር ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል ።
ባለሥልጣኑ አዲስ የወጣውን የመንገድና ትራፊክ መቆጣጣሪያ ደንብ 395 -2009 ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት አሽከርካሪዎች ደንቡን እንዲያውቁት ለማድረግ ሥልጠናውን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የማስተማር ሥራውን እያከናወነ መሆኑ አቶ ካሳሁን አስረድተዋል ።
ከትናንት ጀምሮ ለአሽከርካሪዎች እየተሠጠ ያለው ሥልጠና “ በእኔ ስህተት ምክንያት ሞት ይብቃ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ካሳሁን በአሽከርካሪዎች ስነ ምግባር ጉድለት የሚፈጠሩ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ሁሉም አካላት ሊረባረቡ ይገባል ብለዋል ።
ለህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የሚሠጠው ሥልጠና ቀደም ብሎ በአማራ ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በትግራይ ክልሎች መጀመሩን አቶ ካሳሁን አክለው ገልጸዋል ።
በትራፊክ አደጋዎች ላይ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከሚመዘገቡት የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ 85 በመቶ የሚሆነው በአሽከርካሪዎች የስነምግባር ጉድለት ምክንያት የሚፈጠር ነው ።
የገጠሩን ህብረተሰብ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮችን፣ ወጣትና ሴት አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮችን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ ለ2ኛው የግብርና ዕድገት መርሃ ግብር ምዕራፍ ላይ እቅድ ተይዞ በመሰራት በላይ ይገኛል፡፡
በተለይም የሴቶችና ወጣቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን በማሳደግ ላይ እንደሚገኙ በውይይቱ ተገልጿል፡፡