የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከዝናብና ፀሃይ ለመከላከል የተሠራው ጥላ እንዲነሳ ተጠየቀ ።
ለዋልታ አስተያየታቸውን የሠጡት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ደብር ኃላፊ እንደገለጹት ከዝናብና ፀሃይ ለመከላከል የተሠራው ጥላ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ በማመዘኑ መነሳት እንዳለበት ተናግረዋል ።
የላሊበላ ደብር የቅርስ ክፍል አስተዳዳሪ ደጉ ቀኝ ጌታ በላይ እንደገለጹት ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ጀምሮ ጥላው እንዲነሳ አቤቱታ ብናቀርብም ምላሽ ሳይሠጠን ቆይተናል ብለዋል ።
የላሊበላ መከላከያ ጥላን በተመለከተ በተለያዩ ጊዚያት ባለሙያዎች ጥናት አድርገው ጥላው እንዲነሳ ምክር ቢሠጡም እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉ የሚያሳዝን መሆኑን አስተዳዳሪው ተናግረዋል ።
የላሊበላ ቅርስ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ከመቆጨትና የታሪክ ተጠያቄ ከመሆንም ከወዲሁ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አስተዳዳሪው አጽዕኖት ሠጥተው ተናግረዋል ።
የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን ለመጎብኘት የሚመጣው ቱሪስት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱም ተጠቁሟል ።