ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ የፊታችን ሰኞ ሀምሌ 16 2010 ዓ.ም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር እንደሚወያዩ ታውቋል፡፡

በውይይቱ ላይ ከ45 የመንግሰት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና 4 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ 3 ሺ መምህራን እንደሚሳተፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡

በመደረኩም በተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ እና ምሁራን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ እንደሚወያዩም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

የውይት መድረኩን የትምህርት ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁ ሲሆን ለእያንዳንዱ የትምህርት ተቋም ተሣታፊ መምህራንን በጾታ፣ በትምህርት አይነትና በደረጃ አመጣጥነው መርጠው እንዲልኩ እና ተቋማቱ የተመሰረቱበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ ኮታ እንደተሰጣቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡