የኢትዮ- አሜሪካ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

ስምንተኛው የኢትዮ- አሜሪካ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምክክር መድረኩ በዋናነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ ፣ በመልካም አስተዳደር እና በዲሞክራሲ ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

ውይይቱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ረጀም ጊዜ ያሰቆጠረና በተለያዩ መሰኮች የሚደረግ የሰላምና የደህንነት ጉዳይ  ትብብር አንዱ አካል ነው፡፡

ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በተለይ በአለም አቀፍ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ ይሰራሉ፡፡

ከዚህም ባለፈ በኢኮኖሚ ልማት ጉደይ ላይ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሂዱትን የኢኮኖሚና የእድገት ለውጦችን እንደሚደግፍ እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብሮ በመሰራት ላይ እንሚገኙም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ውይይቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አክሊሉ ሀይለሚካኤል እና በኢትጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሪይነር የተመራ ሲሆን በኢትየጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት እነዲሁም በአገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የሚደረገውን ጥረት የሚያጎለብትም ነው ተብሏል፡፡