የህዳሴ ግድቡ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ ሞተው ተገኙ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ ሞተው ተገኝተዋል፡፡

የኢንጂነር ስመኘው አስክሬን ለምርመራ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል፡፡

የሞታቸውን መንስኤ ለማጣራት የፖሊስ አባላት ምርመራ እያካሄዱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሆስፒታሉ ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤቱን ፖሊስ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል።

ኢንጂነር ስመኘው ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር A29722 ቪ ኤይት መኪናቸው ውስጥ ነው መስቀል አደባባይ ሞተው የተገኙ ሲሆን

የተለያዩ የሀገሪቱ የመንግስት ተቋማት በሞታቸው የሀዘን መግለጫ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡