አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ አዲስ አበባ ገባች

አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ከሁለት አስርት አመታት ቆይታ በኋላ አዲስ አበባ ገባች

በተለያዩ የጥበብ ስራዎቾ የምትታወቀው አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ በርከት ያሉ የዘፈን ግጥሞቿ በታዋቂ አቀንቃኞች ተዘፍነዋል።

ከጥበብ ተለይቼ መኖር አልችልም የምትለው አርቲስቷ በአሜሪካም ጣይቱ የተሰኘ የጥበብ ማዕከል መስርታ መኖርያቸውን በዚያው ያደረጉም ሆነ በእንግድነት ወደ ምድሪቱ ያቀኑ የጥበብ ወዳጆች የጥበብ ፍቅራቸውን እንዲወጡ አድርጋለች።

የግጥም ምሽቶችን ድራማዎችንም በማዘጋጀት የጥበብ ስራዋን ያለዕረፍት ስትከውን እንደነበረም ነው የሚገለፀው ።

በዚህ በጣይቱ የባህል ማዕከል ከ35 በላይ የመድረክ ድራማዎች ከ150 በላይ የግጥም ምሽቶች ማዕከሉ ባለበት ዲሲ አዘጋጅታለች እነዚህን የጥበብ ሰራዎች በ17 የአሜሪካ ግዛቶችም በመዘዋወር አሳይታለች። (ኢቢሲ)