በምስራቅ ሸዋ ዞን ሂሊኮፕተር ተከስክሶ 17 ሰዎች ሞቱ

በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ናናዋ ቀበሌ ዛሬ ከቀኑ 4፡30 አካባቢ ከድሬዳዋ ወደ ቢሾፍቱ 17 ሰዎችን አሳፍሮ ሲበር የነበረ የመከላከያ ሰራዊት ሂሊኮፕተር ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ ሰዎች በሙሉ አልቀዋል፡፡

 

የዞኑ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ እንደገለጹት ኢቲ ኤ አይ ዩ የሚል ጽሁፍ ያለው የመከላከያ ሄሊኮፕተር በመከስከሱ ምክንያት ከሞቱት 17 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ህፃናትና ሁለቱ ሴቶች ናቸው።

 

አውሮኘላኑ የወደቀበት ስፍራም ከሞጆ ከተማ ከአንድ ሰዓት በላይ የእግር መንገድ የሚያስኬድ መሆኑን አስረድተዋል።

 

በቴክኒክ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ የወደቀው አውሮፕላን የአደጋው ዝርዝር መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አመልክተዋል።(ኢዜአ)