የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ነሐሴ 29 ወይም 30 ቀን ይፋ ይሆናል

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት እና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ነሐሴ 29 ወይም 30 ቀን ይፋ ይሆናል።

የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደገለጸው፥ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ነሐሴ 29 እና 30 ይፋ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ በተጠቀሰው ቀን ይፋ እንደሚሆንም ገልጿል።

ኤጀንሲው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የ10ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ የሚናፈሱ ወሬዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውንም አስታውቋል።(ኤፍቢሲ)