በ2011 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተማሪዎችና መምህራን ገለጹ

በ2011 የትምህርት  ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ   በቂ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን  የተለያዩ የአዲስ አበባ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን ገለጹ፡፡

ዋልታ ያነጋገራቸው መምህራን እንደገለጹት በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ካለፉት ጊዜያት  የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ከእቅድዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡

ተማሪዎችም የተጠናቀቀውን የ2010 ክረምት የተለያዩ አጋዥ መጻህፍትን በማንበብ ሲዘጋጁ መቆየታቸው አስረድተዋል፡፡

የ2011  የትምህርት  ዘመን  መስከረም 14 እንደሚጀመራል ተብሎ ቢጠበቀም  አንዳንድ ትምህርት  ቤቶች ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ነገር ግን መደበኛውን የመማር ማስተማር ሂደቱ አለመጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡