የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ለማደስ እና ለመጠገን የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

ስምምነቱን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካይ እና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ተፈራርመዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር በትናንትናው እለት ከፌደራል እና ክልል መንግስታት አመራሮች ጋር በመሆን የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስት ጎብኝተዋል።

በዛሬው እለትም የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ለማደስ እና ለመጠገን የሚያስችል ስምምነት የጅማ ከተማ አመራሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተፈርሟል።

የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ለመጠገን እና ለማደስም የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና የአሜሪካ ኤምባሲ 7 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር መድበው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግስትን ለማደስ የተደረገው ጥናት ሰባት ወራትን የወሰደ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፍ ምሁራን ጥናቱን አካሂደዋል፡፡

የቤተ መንግስቱ እድሳት አስራ ስምት ወራትን የሚፈጅ ሲሆን እድሳቱ እንደተጠናቀቀ ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል፡፡