የአለም ጤና ድርጅት ለኢትዮጵያ የ1 ሚሊየን በላይ የወባ ክትባቶች ድጋፍ አደረገ

የዓለም የጤና ድርጅት በወላይታ ዞን በወባ በሽታ 10 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ   ከ1 ሚሊየን በላይ የወባ ክትባቶችን ድጋፍ  ለኢትዮጵያ መላኩን አስታወቀ።

ድርጅቱ በወላይታ ዞን የቢጫ ወባ በሽታ መቀስቀሱን ማረጋገጡን ጠቁሞ ፥ ከነሐሴ ወር ጀምሮ በ35 ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክት መታየቱን አስታውቋል።

በኦፋ ወረዳ  በሽታው መቀስቀሱን ያመለከተው መረጃው  በጥቅምት ወር አጋማሽ  የክትባት ዘመቻ  ከተካሄደበት ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት የበሽታው ምልክት  እንዳልታየ አስታውቋል።

ድርጅቱ በወረዳው በሽታው በድጋሜ እንዲያገረሽ ሊያደርጉ የሚችሉ መንስኤዎች በመኖራቸውም የአለም ጤና ድርጅት ከክምችት ክፍሉ በአስቸኳይ 1 ነጥብ 45 ሚሊየን  የወባ ክትባቶችን  ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ወስኗል ተብሏል ።

የራስ ምታት፣የጡንቻ ህመም፣ ማስታወክ፣ማቅለሽለሽ እና የድካም ስሜት የቢጫ ወባ በሽታ  የሚያሳያቸው  ምልክቶች  ሲሆኑ በበሽታው ከተጠቁት ሰዎች ግማሽ የሚሆኑት 7 እስከ 10 ቀናት ውስጥ ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል።(ምንጭ: ሮይተርስ)