ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተመድ ምክትል ዋና ጸሃፊን አነጋገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የኤች አይቪ ኤድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተርና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሓፊ ሚሼል ሲዲቤንን አነጋገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመካሄድ ላይ ባለው የማሻሻያ እንቅስቃሴ አማካኝነት አፍሪካንና ኢትዮጵያን በተመለከተ ያለውን ትርክት ለመለወጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አጽንኦት በመስጠት ገልጸዋል፡፡

ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጤና ልማት ጥረትን ለማጠናከር ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር መስማማታቸውም ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)