አንድ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ በተጭበረበረ ቼክ 14 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ሊያወጣ ሲል ተያዘ

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ በተጭበረበረ ቼክ 14 ሚሊየን 724 ሺህ ብር ሊያወጣ ሲል ተያዘ።

ተጠርጣሪው አቶ ገመቹ ጫላ በሚል ስም በባንኩ ቅርንጫፍ ባለፈው አርብ የባንክ ሂሳብ የከፈተ ነው።

ዛሬም ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በማምራት በተጭበረበረ የአምበሳ አውቶብስ ቼክ 14 ሚሊየን ብር 724 ሺህ በማውጣት አርብ እለት ወደ ከፈተው የባንክ ሂሳብ ለማዛወር ሲል በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ተደርጎበት መያዙን መረጃው ያመላክታል።

ተጠርጣሪው በሰዓቱ ለባንኩ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊ 1 ሚሊየን ብር ጉርሻ በማቅረብ እንዲፈፀምለት ለማግባባት ሞክሮ እንደነበርም ተመልክቷል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)