የቀድሞ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዳይሬክቶሬት ጀነራል አቶ ተፈራ መኮንን የአፍሪካ ሲቪል አቪየሽን ኮሚሽን ኃላፊ በመሆን ተመረጡ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሲቪል አቭየሽን ባለስልጣን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል  አቶ ተፈራ መኮንን የአፍሪካ ሲቪል አቭየሽን ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ በመሆን ተመረጡ፡፡

ድርጅቱ ትናንት በዛምቢያ ሊቪንግስተን ውስጥ ባደረገው ስብሰባ በኢትዮጵያ በኩል በዕጩነት የቀረቡት አቶ ተፈራ መኮንን በመምረጣቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደስታውን ገልጿል፡፡

አቶ ተፈራ መኮንን በአቭየሽን ስራ የ37 ዓመት ልምድ ያካበቱ ሲሆን በኬንያ ናይሮቢ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቬየሽን ድርጅት ፕሮጀክት ማኔጀር እንዲሁም በአፍሪካ የሲቪል አቪየሽን ትራንስፖርት ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፡፡ 

በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪየሽን ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ በመሆንም ለስምንት ዓመታት ያክል በካናዳ ሞንቴሪያል ሰርተዋል፡፡(ምንጭ:  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)